9 አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤ብርሃንን እየጠበቀ ይጣ፣የንጋት ጮራ ሲፈነጥቅ አይይ።
10 መከራን ከዐይኔ ይሰውር ዘንድ፣የእናቴን ማሕፀን ደጅ በላዬ አልዘጋምና።
11 “ምነው ገና ስወለድ በጠፋሁ!ምነው ከማሕፀን ስወጣ በሞትሁ!
12 የሚቀበሉኝ ጒልበቶች፤የሚያጠቡኝ ጡቶች ለምን ተገኙ?
13 ይህን ጊዜ በሰላም በተኛሁ፣አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤
14 አሁን ፈርሶ የሚታየውን ስፍራ ለራሳቸው ካሠሩት፣ከምድር ነገሥታትና ከአማካሪዎች ጋር፣
15 ቤታቸውን በብር ከሞሉ፣ወርቅም ከነበራቸው ገዦች ጋር ባረፍሁ ነበር።