12 በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ።
13 መንገድ ዘጉብኝ፤የሚገታቸው ሳይኖር፣ሊያጠፉኝ ተነሡ።
14 በሰፊ ንቃቃት ውስጥ እንደሚመጣ ሰው መጡብኝ፤በፍርስራሽም መካከል እየተንከባለሉ ደረሱብኝ።
15 በድንጋጤ ተውጫለሁ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዶአል፤በሰላም መኖሬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቶአል።
16 “አሁን ነፍሴ በውስጤ አለቀች፤የመከራ ዘመንም ይዞኛል።
17 ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም።
18 እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዶአል፤በልብሴም ክሳድ አንቆ ይዞኛል።