15 በድንጋጤ ተውጫለሁ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዶአል፤በሰላም መኖሬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቶአል።
16 “አሁን ነፍሴ በውስጤ አለቀች፤የመከራ ዘመንም ይዞኛል።
17 ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም።
18 እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዶአል፤በልብሴም ክሳድ አንቆ ይዞኛል።
19 እርሱ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤እኔም ከዐፈርና ከዐመድ አልተሻልሁም።
20 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ።
21 ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ።