2 ጒልበት የከዳቸው፤የክንዳቸው ብርታት ምን ፋይዳ ይሞላልኝ ነበር?
3 ከችጋርና ከራብ የተነሣ ጠወለጉ፤ሰው በማይኖርበት በረሓ፣በደረቅም ምድር በሌሊት ተንከራተቱ።
4 ከቍጥቋጦ ምድር ጨው ጨው የሚል አትክልት ለቀሙ፤ምግባቸውም የክትክታ ሥር ነበር።
5 ከኅብረተ ሰቡ ተለይተው ተባረሩ፤ሰዎች እንደ ሌባ ይጮኹባቸዋል።
6 በዐለት መካከል በምድር ጒድጓድ፣በደረቅ ሸለቆ ዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዱ።
7 በጫካ ውስጥ ያናፋሉ፤በእሾሃማ ቍጥቋጦ መካከልም ይታፈጋሉ።
8 ስማቸው የማይታወቅ አልባሌ ናቸው፤ከምድሪቱም ተባረዋል።