1 “ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።
2 ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰው ዕድል ፈንታው፣ከአርያም ሁሉን ከሚችል አምላክስ ዘንድ ቅርሱ ምንድ ነው?
3 ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን?
4 እርሱ መንገዴን አያይምን?እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
5 “በሐሰት ሄጄ እንደሆነ፣እግሬም ወደ ሽንገላ ቸኵሎ ከሆነ፣
6 እግዚአብሔር በእውነተኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ።