11 ይህ አሳፋሪ፣ፍርድም የሚገባው ኀጢአት ነውና።
12 ይህ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ እሳት ነው፤ቡቃያዬንም ባወደመ ነበር።
13 “ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ፣ፍርድ አዛብቼ ከሆነ፣
14 እግዚአብሔር ሲነሣ ምን አደርጋለሁ?ሲጠይቀኝስ ምን መልስ እሰጣለሁ?
15 እኔን በማሕፀን ውስጥ የፈጠረኝ እነርሱን የፈጠረ አይደለምን?በሆድ ውስጥ የሠራንስ እርሱ ራሱ አይደለምን?
16 “ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣
17 እንጀራዬን ከድኻ አደጉ ጋር ሳልካፈል፣ለብቻዬ በልቼ ከሆነ፣