3 ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን?
4 እርሱ መንገዴን አያይምን?እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
5 “በሐሰት ሄጄ እንደሆነ፣እግሬም ወደ ሽንገላ ቸኵሎ ከሆነ፣
6 እግዚአብሔር በእውነተኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ።
7 አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣
8 የዘራሁትን ሌላ ይብላው፤ሰብሌም ተነቅሎ ይጥፋ።
9 “ልቤ ሌላዋን ሴት ከጅሎ፣በባልንጀራዬ ደጅ አድብቼ ከሆነ፣