1 “አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤የምለውንም ሁሉ አድምጥ።
2 እንግዲህ አፌን እከፍታለሁ፤አንደበቴም ይናገራል።
3 ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል።
4 የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።