16 በጆሯቸው ይናገራል፤በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤
17 ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ከትዕቢት ይጠብቃል፤
18 ነፍሱን ከጒድጓድ፤ሕይወቱንም ከሰይፍ ጥፋት ያድናል።
19 ደግሞም ሰው ታሞ በዐልጋው ላይ ሳለ፣በዐጥንቱ የዘወትር ሥቃይ ይገሥጸዋል፤
20 ያኔም ሕይወቱ መብልን ትጠላለች፤ነፍሱም ምርጥ ምግብን ትጠየፋለች።
21 እንዳልነበረ ሆኖ ሥጋው ይመነምናል፤ተሸፍኖ የነበረው ዐጥንቱም ገጦ ይወጣል።
22 ነፍሱ ወደ ጒድጓድ፣ሕይወቱም ወደ ሞት መልእክተኞች ትቀርባለች።