21 እንዳልነበረ ሆኖ ሥጋው ይመነምናል፤ተሸፍኖ የነበረው ዐጥንቱም ገጦ ይወጣል።
22 ነፍሱ ወደ ጒድጓድ፣ሕይወቱም ወደ ሞት መልእክተኞች ትቀርባለች።
23 “ሆኖም ትክክለኛውን መንገድ ለሰው ያመለክት ዘንድ፣መካከለኛም ይሆንለት ዘንድ፣ከሺህ አንድ መልአክ ቢገኝ፣
24 ለሰውየውም በመራራት፣‘ቤዛ አግኝቼለታለሁና፣ወደ ጒድጓድ እንዳይወርድ አድነው’ ቢለው፣
25 በዚህ ጊዜ ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል።
26 ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ሞገስም ያገኛል፤የእግዚአብሔርን ፊት ያያል፤ ሐሤትም ያደርጋል፤እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ቦታው ይመልሰዋል።
27 ከዚያም ወደ ሰዎች መጥቶ እንዲህ ይላል፤‘ኀጢአትን ሠርቻለሁ፤ ትክክል የሆነውን አጣምሜአለሁ፤ነገር ግን የእጄን አላገኘሁም።