4 የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።
5 የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም።
6 በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንዳንተው ነኝ፤የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው።
7 እኔን መፍራት የለብህም፤እጄም ሊከብድብህ አይገባም።
8 “በእርግጥ የተናገርኸውን ሰምቻለሁ፤እንዲህም ስትል አድምጫለሁ፤
9 ‘ኀጢአት የሌለብኝ ንጹሕ ነኝ፤ከበደል ነጻ ነኝ፤ እድፈትም የለብኝም፤
10 እግዚአብሔር ግን ሰበብ ፈልጎብኛል፤እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል፤