8 “በእርግጥ የተናገርኸውን ሰምቻለሁ፤እንዲህም ስትል አድምጫለሁ፤
9 ‘ኀጢአት የሌለብኝ ንጹሕ ነኝ፤ከበደል ነጻ ነኝ፤ እድፈትም የለብኝም፤
10 እግዚአብሔር ግን ሰበብ ፈልጎብኛል፤እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል፤
11 እግሬን በግንድ አጣብቆአል፤እንቅስቃሴዬንም ሁሉ ይከታተላል።’
12 “ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ስለሚበልጥ፣ትክክል እንዳልሆንህ እነግርሃለሁ።
13 የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ለምን ታማርርበታለህ?
14 ሰው ባያስተውለውም፣እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤