17 ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን?አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ?
18 ነገሥታትን ‘የማትረቡ ናችሁ፣’መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’የሚላቸው እርሱ አይደለምን?
19 ሁሉም የእጁ ሥራ ስለሆኑ፣እርሱ ለገዦች አያደላም፤ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።
20 እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።
21 “ዐይኖቹ የሰውን አካሄድ ይመለከታሉ፤ርምጃውንም ሁሉ ይከታተላሉ።
22 ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፣ጨለማ ስፍራ ወይም የሞት ጥላ የለም።
23 ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።