23 ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።
24 ያለ ምንም ጥያቄ ኀያላንን ያንኰታኵታል፤ሌሎችንም በቦታቸው ይሾማል።
25 እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤እነርሱም ይደቃሉ።
26 ስለ ክፋታቸውም፣በሰው ሁሉ ፊት ይቀጣቸዋል፤
27 እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፤መንገዱንም ችላ ብለዋል።
28 የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤የመከረኞችን ጩኽት ሰማ።
29 እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል?እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤