25 እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤እነርሱም ይደቃሉ።
26 ስለ ክፋታቸውም፣በሰው ሁሉ ፊት ይቀጣቸዋል፤
27 እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፤መንገዱንም ችላ ብለዋል።
28 የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤የመከረኞችን ጩኽት ሰማ።
29 እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል?እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤
30 ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።
31 “ሰው ለእግዚአብሔር እንዲህ ቢል፣ የተሻለ ነበር፤‘እኔ በደለኛ ነኝ፤ ከእንግዲህ ግን አልበድልም፤