30 ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።
31 “ሰው ለእግዚአብሔር እንዲህ ቢል፣ የተሻለ ነበር፤‘እኔ በደለኛ ነኝ፤ ከእንግዲህ ግን አልበድልም፤
32 ማየት ያልቻልሁትን አስተምረኝ፤ኀጢአት ሠርቼ እንደሆነም፣ ደግሜ አልሠራም።’
33 ታዲያ አንተ ለመናዘዝ ፈቃደኛ ሳትሆን፤እግዚአብሔር እንደ ወደድህ ይከፍልሃልን?መወሰን ያለብህ አንተ ነህ እንጂ፣ እኔ አይደለሁም፤እንግዲህ የምታውቀውን ንገረኝ።
34 “አስተዋዮች ይናገራሉ፤የሚሰሙኝም ጠቢባን እንዲህ ይሉኛል፤
35 ‘ኢዮብ ያለ ዕውቀት ይናገራል፤ቃሉም ማስተዋል ይጐድለዋል።’
36 ምነው ኢዮብ እስከ መጨረሻ በተፈተነ ኖሮ!እንደ ክፉ ሰው መልሶአልና፤