4 የሚበጀንን እንምረጥ፣መልካሙንም አብረን እንወቅ።
5 “ኢዮብ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤እግዚአብሔር ግን ፍትሕ ነሣኝ፤
6 እውነተኛ ብሆንም፣እንደ ውሸታም ተቈጥሬአለሁ፤በደል ባይኖርብኝም፣በማይፈወስ ቍስል ተመትቻለሁ።’
7 ፌዝን እንደ ውሃ የሚጠጣት፣እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?
8 ከክፉ አድራጊዎች ጋር ይተባበራል፤ከኀጢአተኞችም ጋር ግንባር ይፈጥራል።
9 ‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሎአልና።
10 “ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣በደልንም መፈጸም ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።