9 ‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሎአልና።
10 “ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣በደልንም መፈጸም ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።
11 ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፤እንደ አካሄዱም ይከፍለዋል።
12 በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤ሁሉን የሚችል አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።
13 ምድርን እንዲገዛ የሾመው አለን?የዓለምስ ሁሉ ባለቤት ያደረገው ማን ነው?
14 እርሱ መንፈሱን መልሶ ቢወስድ፣እስትንፋሱንም ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣
15 ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።