13 “ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም።
14 በቤተ ጣዖት ውስጥ ዝሙት በሚፈጽሙት መካከል፣ገና በወጣትነታቸው ይቀጫሉ።
15 ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።
16 “አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።
17 አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኖአል፤ፍርድና ብይን ይዘውሃል።
18 ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።
19 ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?