17 አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኖአል፤ፍርድና ብይን ይዘውሃል።
18 ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።
19 ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?
20 ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ሌሊት አትመኝ።
21 ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22 “እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሎአል፤እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23 እርሱን መንገድ የሚመራው፣ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?