20 ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ሌሊት አትመኝ።
21 ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22 “እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሎአል፤እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23 እርሱን መንገድ የሚመራው፣ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?
24 ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።
25 ሰው ሁሉ አይቶታል፤ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።
26 እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው!የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።