24 ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።
25 ሰው ሁሉ አይቶታል፤ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።
26 እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው!የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።
27 “የውሃን ነጠብጣብ ወደ ላይ ያተናል፤መልሶም በዝናብ መልክ በጅረቶች ላይ ያወርዳል፤
28 ደመናት ጠል ያንጠባጥባሉ፤ዶፍም በሰው ላይ ይወርዳል።
29 ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጒድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
30 መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት፤የባሕሩንም ወለል ይሸፍናል።