6 ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።
7 ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
8 ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
9 በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣ተግባራቸውን ይነግራቸዋል።
10 ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዛቸዋል።
11 ታዘው ቢያገለግሉት፣ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣ዕድሜያቸውንም በርካታ ይፈጽማሉ።
12 ባይሰሙ ግን፣በሰይፍ ይጠፋሉ፤ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።