8 ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
9 በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣ተግባራቸውን ይነግራቸዋል።
10 ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዛቸዋል።
11 ታዘው ቢያገለግሉት፣ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣ዕድሜያቸውንም በርካታ ይፈጽማሉ።
12 ባይሰሙ ግን፣በሰይፍ ይጠፋሉ፤ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።
13 “ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም።
14 በቤተ ጣዖት ውስጥ ዝሙት በሚፈጽሙት መካከል፣ገና በወጣትነታቸው ይቀጫሉ።