5 የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጒዳል፤እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል።
6 በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል።
7 እርሱ የፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ ሥራውን ያውቁ ዘንድ፣እያንዳንዱ ሰው እንዳይሠራ ይገታዋል።
8 እንስሳት ይጠለላሉ፤በየዋሻቸውም ይቈያሉ።
9 ዐውሎ ነፋስ ከማደሪያው፣ብርድም ከብርቱ ነፋስ ይወጣል።
10 የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።
11 ደመናትን ርጥበት ያሸክማቸዋል፤መብረቁንም በውስጣቸው ይበትናል።