7 እርሱ የፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ ሥራውን ያውቁ ዘንድ፣እያንዳንዱ ሰው እንዳይሠራ ይገታዋል።
8 እንስሳት ይጠለላሉ፤በየዋሻቸውም ይቈያሉ።
9 ዐውሎ ነፋስ ከማደሪያው፣ብርድም ከብርቱ ነፋስ ይወጣል።
10 የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።
11 ደመናትን ርጥበት ያሸክማቸዋል፤መብረቁንም በውስጣቸው ይበትናል።
12 ያዘዘውን ለመፈጸም፣እርሱ በሚሰጠው መመሪያ፣በመላው የምድር ገጽ ላይ ይሽከረከራሉ።
13 ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል።