1 እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤
2 “ዕውቀት በጐደለው ቃል፣ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው?
3 እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ ልጠይቅህ፣አንተም መልስልኝ።
4 “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።