15 ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሮአል።
16 “ወደ ባሕር ምንጭ ወርደህ ታውቃለህን?ወይስ ወደ ጥልቀቱ ገብተህ በመሠረቱ ላይ ተመላልሰሃልን?
17 የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን?የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን?
18 የምድርን ስፋት ታውቃለህን?ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ።
19 “ወደ ብርሃን መኖሪያ የሚያደርሰው መንገድ የትኛው ነው?የጨለማ መኖሪያስ ወዴት ነው?
20 ወደ ማደሪያቸው ልትወስዳቸው ትችላለህን?የመኖሪያቸውን መንገድ ታውቃለህ?
21 ያን ጊዜ ተወልደሃል! ዕድሜህ ትልቅ ነውና፣አንተስ በእርግጥ ሳታውቅ አትቀርም!