12 እህልህን እንዲሰበስብልህ፣በዐውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ ታምነዋለህን?
13 “ሰጎን ክንፎቿን በደስታ ታራግባለች፤ነገር ግን እንደ ሽመላ ላባዎች ሊሆኑ አይችሉም።
14 ዕንቍላሏን መሬት ላይ ትጥላለች፤እንዲሞቅም በአሸዋ ውስጥ ትተወዋለች።
15 እግር እንደሚሰብረው፤የዱር አውሬም እንደሚረግጠው አታስብም።
16 የእርሷ እንዳልሆኑ ሁሉ በልጆቿ ትጨክናለች፤ድካሟም በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም፤
17 እግዚአብሔር ጥበብ ነሥቶአታልና፤ማስተዋልንም አልሰጣትም።
18 ለመሸምጠጥም ክንፎቿን ስትዘረጋ፣በፈረስና በጋላቢው ትሥቃለች።