17 እግዚአብሔር ጥበብ ነሥቶአታልና፤ማስተዋልንም አልሰጣትም።
18 ለመሸምጠጥም ክንፎቿን ስትዘረጋ፣በፈረስና በጋላቢው ትሥቃለች።
19 “ለፈረስ ጒልበትን ትሰጠዋለህን?ዐንገቱንስ ጋማ ታለብሰዋለህን?
20 እንደ አንበጣ የምታስዘልለው አንተ ነህን?የማንኰራፋቱም ገናናነት አስፈሪ ነው።
21 በጒልበቱ እየተመካ በብርቱ ይጐደፍራል፤ጦርነት ሊገጥም ይወጣል።
22 ያለ አንዳች ሥጋት፣ በፍርሀት ላይ ይሥቃል፤ሰይፍ ቢመዘዝበትም ወደ ኋላ አይልም።
23 ከሚብረቀረቀው ጦርና አንካሴ ጋር፣የፍላጻው ኮረጆ ጐኑ ላይ ይንኳኳል።