24 በወኔ መሬቱን እየጐደፈረ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤የመለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል።
25 መለከቱ ሲያንባርቅ፣ ‘እሰይ’ ይላል፤የአዛዦችን ጩኸትና የሰራዊቱን ውካታ፣ጦርነትንም ከሩቅ ያሸታል።
26 “ጭልፊት የሚበረው፣ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው፣ በአንተ ጥበብ ነውን?
27 ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ጎጆውንም በከፍታ ላይ የሚሠራው፣በአንተ ትእዛዝ ነውን?
28 በገደል ላይ ይኖራል፤ በዚያም ያድራል፤ምሽጉም የቋጥኝ ጫፍ ነው።
29 እዚያ ሆኖ የሚነጥቀውን ይቃኛል፤ዐይኑም ከሩቅ አጥርቶ ያያል።
30 ጫጩቶቹ ደም ይጠጣሉ፤እርሱም በድን ካለበት አይታጣም።”