4 ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም።
5 “ለሜዳ አህያ ነጻነት የሰጠው ማን ነው?እስራቱንስ ማን ፈታለት?
6 ምድረ በዳውን መኖሪያው፣የጨውንም ምድር ማደሪያው አድርጌ ሰጠሁት።
7 በከተማ ውካታ ይሥቃል፤የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።
8 በየተራራው ይሰማራል፤ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል።
9 “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን?በበረትህስ አጠገብ ያድራልን?
10 እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ?ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጒልልሃልን?