6 ምድረ በዳውን መኖሪያው፣የጨውንም ምድር ማደሪያው አድርጌ ሰጠሁት።
7 በከተማ ውካታ ይሥቃል፤የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።
8 በየተራራው ይሰማራል፤ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል።
9 “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን?በበረትህስ አጠገብ ያድራልን?
10 እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ?ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጒልልሃልን?
11 ጒልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ?ከባዱን ሥራህንስ ለእርሱ ትተዋለህ?
12 እህልህን እንዲሰበስብልህ፣በዐውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ ታምነዋለህን?