1 ቴማናዊው ኤልፋዝም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2 “አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን?ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል?
3 እነሆ፤ አንተ ብዙዎችን ታስተምር እንደ ነበር አስብ፤የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፤
4 ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤የሚብረከረከውንም ጒልበት ታጸና ነበር።
5 አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም።
6 እግዚአብሔርን መፍራት መታመኛህ፣ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?