ኢዮብ
ምዕራፎች 4:6-12
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
6እግዚአብሔርን መፍራት መታመኛህ፣ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?
7“አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ፣ ማን ነው?ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ?
8እኔ እንዳየሁ፣ ክፋትን የሚያርሱ፣መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።
9በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።
10አንበሳ ያገሣል፤ ቍጡውም አንበሳ ይጮኻል፤የደቦል አንበሳው ጥርስ ግን ተሰብሮአል።
11ብርቱው አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፤የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።
12“ቃል በምስጢር መጣልኝ፤ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።