7 “አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ፣ ማን ነው?ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ?
8 እኔ እንዳየሁ፣ ክፋትን የሚያርሱ፣መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።
9 በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።
10 አንበሳ ያገሣል፤ ቍጡውም አንበሳ ይጮኻል፤የደቦል አንበሳው ጥርስ ግን ተሰብሮአል።
11 ብርቱው አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፤የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።
12 “ቃል በምስጢር መጣልኝ፤ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።
13 በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣