13 ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን።
14 እኔም ቀኝ እጅህ እንደምታድንህ፣በዚያን ጊዜ አረጋግጬ እቀበላለሁ።
15 “አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን፣‘ብሄሞት’ ተመልከት፤እንደ በሬ ሣር ይበላል፤
16 ብርታቱ ወገቡ ውስጥ፣ኀይሉም በሆዱ ጡንቻ ላይ ነው።
17 ጅራቱ እንደ ጥድ ዛፍ ይወዛወዛል፤የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው።
18 ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።
19 እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው።