5 አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።”
6 እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ፣ ለኢዮብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤
7 “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤አንተም መልስልኝ።
8 “ፍርዴን ታቃልላለህን?ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ?
9 እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን?ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጒድ ይችላልን?
10 እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤
11 ቍጣህን አፍስስ፤ትዕቢተኛውን ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው፤