8 “ፍርዴን ታቃልላለህን?ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ?
9 እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን?ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጒድ ይችላልን?
10 እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤
11 ቍጣህን አፍስስ፤ትዕቢተኛውን ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው፤
12 ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው፤ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው።
13 ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን።
14 እኔም ቀኝ እጅህ እንደምታድንህ፣በዚያን ጊዜ አረጋግጬ እቀበላለሁ።