1 “ሌዋታንን በመንጠቆ ልታወጣው፣ወይም ምላሱን በገመድ ልታስረው ትችላለህን?
2 መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ወይም ጒንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?
3 እርሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል?በለስላሳ ቃላትስ ይናገርሃል?
4 ለዘላለም ባሪያ ታደርገው ዘንድ፣ከአንተ ጋር ይዋዋላልን?
5 እንደ ወፍ አልምደኸው ከእርሱ ጋር ልትጫወት ትችላለህ?ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን?
6 ነጋዴዎችስ በእርሱ ላይ ይከራከራሉን?ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል?