10 ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፤ማን ፊቱ ሊቆም ይችላል?
11 ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው?ከሰማይ በታች ማንም የለም።
12 “ስለ ብርታቱና ስለ አካላቱ ውበት፣ስለ እጅና እግሩ ከመናገር አልቈጠብም።
13 የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል?ማንስ ሊለጒመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?
14 አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን፣የአፉን ደጅ ማን ደፍሮ ይከፍታል?
15 ጀርባው፣ አንድ ላይ የተጣበቁ፣የጋሻ ረድፎች አሉት፤
16 እጅግ የተቀራረቡ ስለሆኑ፣ነፋስ በመካከላቸው አያልፍም፤