17 እርስ በርስ የተገጣጠሙ ናቸው፤አንዱ ከአንዱ ጋር ተጣብቆአልና ማንም ሊለያያቸው አይችልም።
18 እንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ያወጣል፤ዐይኖቹም እንደ ማለዳ ጮራ ናቸው።
19 ከአፉ ፍም ይወጣል፤የእሳት ትንታግ ይረጫል።
20 በሸምበቆ ማገዶ ላይ ከተጣደ ድስት እንደሚወጣ እንፋሎት፣ከአፍንጫው ጢስ ይትጐለጐላል።
21 እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል።
22 ብርታት በዐንገቱ ውስጥ አለ፤አሸባሪነትም በፊቱ እመር እመር ይላል።
23 የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ፣በላዩ የጸናና ከቦታው የማይናጋ ነው።