2 መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ወይም ጒንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?
3 እርሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል?በለስላሳ ቃላትስ ይናገርሃል?
4 ለዘላለም ባሪያ ታደርገው ዘንድ፣ከአንተ ጋር ይዋዋላልን?
5 እንደ ወፍ አልምደኸው ከእርሱ ጋር ልትጫወት ትችላለህ?ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን?
6 ነጋዴዎችስ በእርሱ ላይ ይከራከራሉን?ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል?
7 ቈዳው ላይ አንካሴ ልትሰካ፣ጭንቅላቱንም በዓሣ መውጊያ ጦር ልትበሳ ትችላለህን?
8 እርሱን እስቲ ንካው፣ግብግቡን ታስታውሳለህ፤ ከቶም አያላምድህም።