23 የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ፣በላዩ የጸናና ከቦታው የማይናጋ ነው።
24 ደረቱ እንደ ዐለት የጠጠረ፣እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጠነከረ ነው።
25 እርሱ በተነሣ ጊዜ፣ ኀያላን ይርዳሉ፤በሚንቀሳቀስበትም ጊዜ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።
26 ጦር፣ ፍላጻ ወይም አንካሴ፣ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።
27 እርሱ ብረትን እንደ አገዳ፣ናስንም እንደ ነቀዘ ዕንጨት ይቈጥራል።
28 ቀስት አያባርረውም፤የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።
29 ቈመጥ በእርሱ ፊት እንደ ገለባ ነው፤ጦር ሲሰበቅ ይሥቃል።