7 ቈዳው ላይ አንካሴ ልትሰካ፣ጭንቅላቱንም በዓሣ መውጊያ ጦር ልትበሳ ትችላለህን?
8 እርሱን እስቲ ንካው፣ግብግቡን ታስታውሳለህ፤ ከቶም አያላምድህም።
9 እርሱን በቍጥጥር ሥር አውላለሁ ማለት ዘበት ነው፤በዐይን ማየት እንኳ ብርክ ያስይዛል።
10 ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፤ማን ፊቱ ሊቆም ይችላል?
11 ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው?ከሰማይ በታች ማንም የለም።
12 “ስለ ብርታቱና ስለ አካላቱ ውበት፣ስለ እጅና እግሩ ከመናገር አልቈጠብም።
13 የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል?ማንስ ሊለጒመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?