1 ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤
2 “አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።
3 አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው’ አልኸኝ፤በእርግጥ ያልገባኝን ነገር፣የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጒዳይ ተናገርሁ።
4 “ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ።