14 ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።
15 ችግረኛውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል።
16 ስለዚህ ድኻ ተስፋ አለው፤ዐመፅም አፏን ትዘጋለች።
17 “እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።
18 እርሱ ያቈስላል፤ ይፈውሳል፤እርሱ ይሰብራል፤ በእጁም ይጠግናል፤
19 እርሱ ከስድስት መቅሠፍት ይታደግሃል፤በሰባተኛውም ጒዳት አያገኝህም።
20 በራብ ጊዜ ከሞት፣በጦርነትም ከሰይፍ ያድንሃል።