8 “እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ጒዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።
9 እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።
10 ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል።
11 የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል።
12 እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።
13 ጠቢባንን በጥበባቸው ይይዛል፤የተንኰለኞችንም ሤራ ያጠፋል።
14 ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።