11 “አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?
12 የድንጋይ ጒልበት አለኝን?ሥጋዬስ ናስ ነውን?
13 ያልተሳካልኝ ሰው ነኝና፣ራሴን ለመርዳት ምን ጒልበት አለኝ?
14 “ለወዳጁ በጎነት የማያሳይ ሰው፣ሁሉን የሚችለውን አምላክ መፍራት ትቶአል።
15 ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤
16 በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤
17 በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።