4 ሁሉን የሚችል አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል።
5 የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?
6 የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን?ወይስ የዕንቍላል ውሃ ጣዕም አለውን?
7 እንዲህ ዐይነቱን ምግብ እጸየፋለሁ፤ለመንካትም አልፈልግም።
8 “ምነው ልመናዬ በተመለሰልኝ፤እግዚአብሔር የምመኘውን በሰጠኝ፤
9 እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣ምነው እጁ በተፈታ!
10 ፋታ በማይሰጥ ሕመም ውስጥ እየተደሰትሁ፣ይህ መጽናኛ በሆነልኝ ነበር፤የቅዱሱን ትእዛዝ አልጣስሁምና።